ባለፉት 24 ሰአታት 902 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ 7 ሰዎች ህይወት አልፏል
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ6 ሺህ 668 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 902 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታወቁ፡፡
ባለፉት 24 ሰዓታት ከቫይረሱ ጋር ተያይዞ 7 ሰዎች ህይወት ማለፉንም ሚኒስትሯ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
ሚኒስትሯ በገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ 253 ሰዎች በፅኑ ህክምና ላይ እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም 764ሰዎች ከቫይረሱ ሲያገግሙ ይህን ተከትሎም ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 36 ሺህ 434 ደርሷል፡፡
ከዚህ ባለፈ እስካሁን በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥርም 1 ሺህ 262 መድረሱን ገልጸዋል፡፡
እስካሁን በኢትዮጵያ ለ1 ሚሊየን 327 ሺህ 832 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎላቸዋል።