Fana: At a Speed of Life!

33 ሚሊየን ብር የሚገመት ኮቪድ 19ን ለመከላከል የሚያግዝ የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ግሎባል ላይፍ ሼሪንግ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት 33 ሚሊየን ብር የሚገመት ኮቪድ 19ን ለመከላከል የሚያግዙ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች እና ለኮቪድ 19 መከላከል የሚውሉ አልባሳትን ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ አደረገ፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ በደቡብ ኮሪያ የሚገኘው ይህ ግብረ ሰናይ ድርጅት ያደረገውን ድጋፍ አስመልክተው እንዳሉት የተደረገው ድጋፍ ኢትዮጵያ ያለችበትን ፈታኝ ጊዜ ለመወጣት እና እንደሀገር ለሚሰራው ስራ ቁልፍ ሚና እንዳለው ተናግረዋል፡፡
የተደረገው ልገሳም ለኮቪድ19 ምላሽ ብቻ ሳይሆን ለመደበኛ የጤና አገልግሎቶችን ለማጠናከር የሚያግዝ ነው ብለዋል ፡፡
የግሎባል ላይፍ ሼሪንግ ተወካይ ዶክተር ዮዲት አብርሃ ድጋፉ የሃገሪቱን የጤና ዘርፍ ፍላጎት መሰረት በማድረግ የተበረከተ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡
ድጋፉ 29 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ልዩ ልዩ መድሃኒቶች፣ 3 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የህክምና መገልገያዎች ለኮቪድ 19 መከላከያ የሚያግዙ አልባሳት እና 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ለመደበኛ የጤና አገልግሎት የሚውሉ የህክምና መሳሪያዎችን የሚያጠቃል መሆኑን ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.