Fana: At a Speed of Life!

በኮቪድ-19 ምክንያት በጊዜያዊነት የአትክልት መሸጫ የሆነውን ጃን ሜዳን ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ መስከረም 29፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በኮቪድ-19 ምክንያት በጊዜያዊነት የአትክልት መሸጫ የሆነውን ጃን ሜዳን ወደ ቀድሞ አገልግሎቱ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገለፀ፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የጃን ሜዳ የአትክልት መሸጫ ስፍራን ጎብኝተዋል።
በጉብኝቱ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለፁት በኮቪድ-19 ምክኒያት ፒያሳ የነበረውን የአትክልት መሸጫ በመዝጋት በጊዜያዊነት ለአትክልት መገበያያነት እንዲያገለግል መደረጉን አስታውሰዋል፡፡
ከተማ አስተዳደሩ የጃንሜዳ አትክልት መገበያያ ቦታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ነፃ ለማድረግ እና ሌሎች ተለዋጭ የገበያ ማዕከላት ግንባታ በፍጥነት ለማካሄድ በዝግጅት ላይ መሆኑን አቶ ጃንጥራር ተናግረዋል፡፡
መላው የንግዱ ማህበረሰብና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም ዘላቂ እና ዘመናዊ የግብይት ስርአት ለመዘርጋት በሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ አስተባባሪው ጥሪ ማቅረባቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.