Fana: At a Speed of Life!

በታይላንድ አውቶቡስ እና ባቡር ተጋጭተው በደረሰ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት አለፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 1 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በታይላንድ አውቶቡስ እና ባቡር ተጋጭተው በደረሰ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት ማለፉን የሀገሪቱ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።
አደጋው ዛሬ ማለዳ በምስራቃዊ ባንኮክ 50 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የደረሰ ሲሆን÷ በዚህ አደጋ ለህልፈት ከተዳረጉት ሰዎች በተጨማሪ በርካቶች በአደጋው መጎዳታቸው ተገልጿል።
በወቅቱም በአውቶብሱ ውስጥ የነበሩ 60 ተሳፋሪዎች የቡድሂስት ጾም መጨረሻን ለማሰብ ወደ ቤተመቅደስ እየሄዱ እንደነበረም ተነግሯል።
ሆኖም አውቶብሱ ሃዲድ አቋርጦ ለማለፍ በሚሞክርበት ሰዓት ከምስራቃዊ የሃገሪቱ ክፍል ወደ ባንኮክ ይመጣ በነበረ ባቡር መገጨቱ ተነግሯል።
በአደጋው አውቶቡሱ ላይ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት ከስፍራው የወጡ ምስሎች አሳይተዋል።
አደጋውን ተከትሎ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ፕራዩት ቻን ኦቻ የሀዘን መግለጫ ያወጡ ሲሆን ÷ የአደጋውን መንስዔ የሚያጣራ ጥልቅ ምርመራ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።
በታይላንድ በደካማ የመንገድ መሰረተ ልማትና የተጨናነቁ የትራፊክ መንገዶች እንደነዚህ አይነት አደጋዎች የተለመዱ መሆናቸው ይነገራል።
የዓለም የጤና ድርጅት የ 2018 ባወጣው ሪፖርቱ በዓለም ላይ በትራፊክ አደጋ በሚከሰት ሞት ታይላንድን በሁለተኝነት አስቀምጧታል።
ምንጭ፡- ቢቢሲ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.