Fana: At a Speed of Life!

ለሚፈለገው ብሄራዊ መግባባት ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባል- የፓለቲካ ፓርቲዎችና የታሪክ ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ለሚፈለገው ብሄራዊ መግባባት ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ እንደሚገባ የፓለቲካ ፓርቲዎች እና የታሪክ ምሁራን ተናገሩ።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የፓለቲካ ፓርቲዎች እና የታሪክ ምሁራን÷ ፓርቲዎች ከመገፋፋት እና መጎሻሽም ወጥተው ዜጎች ለሚፈልጓት የተረጋጋች ሃገር ወደ ተሻለው የውይይት መስመር ለመምጣት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።
ጫፍ የረገጡ የሃሳብ ልዩነቶችን ለማቀራረብ በፓለቲካ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው፣ የታሪክ ምሁራን እና በሌሎች ሙያ ላይ የተሰማሩ ዜጎች ወደ ሃሳብ ማእድ ቀርበው ይነጋገሩ ዘንድም ሁሉም ሃላፊነቱን ሊወጣ ይገባልም ነው ያሉት።
የነጻነትና እኩልነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶክተር አብዱል ቃድር አደም እና የመኢአድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ መሉ ጌታ አበበ÷ አሁን ላይ የተጀመሩ እና ሃገራዊ መግባባትን ለመፍጠር የሚያግዙ ውይይቶች ወሳኝ እንደሆኑ ተናግረዋል።
የታሪክ እና ባህል ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር አህመድ ዘከርያ በበኩላቸዉ ÷ የሀገሪቱ ልሂቃን ሃሳባቸውን ወደ ጠረጴዛ ዙሪያ አምጥተዉ ለሃገር የሚበጅ ስራ ለመስራት ሊተጉ ይገባል ብለዋል።
በአወል አበራ
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.