Fana: At a Speed of Life!

የቱሪዝም ዘርፉን ዳግም ለማስጀመር አዲስ የፕሮቶኮል መመሪያ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረውን የቱሪዝም ዘርፍ ዳግም ለማስጀመር አዲስ የፕሮቶኮል መመሪያ ይፋ መሆኑ ተገለፀ፡፡
የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ዛሬ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ሀገር አቀፍ አስጎብኚዎች የፕሮቶኮል መመሪያውን ይፋ ያደረገ ሲሆን÷ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ያደረሰውን ኢኮኖሚያዊ ተፅዕኖ ታሳቢ በማድረግ እና በቱሪዝሙ የተሻለ እንቅስቃሴ እንዲኖር በጤና ሚኒስቴር የተቀመጡ ጥንቃቄዎችን በመተግበር ወደ ሰራ ይገባል ተብሏል::
በዚህም በተለይ አስጎብኚ ድርጅቶች፣ አሽከርካሪዎች፣ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አና የመስህብ ስፍራዎች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ ወደ ስራ መግባት እንዳለባቸው በመመሪያው ተቀምጧል።
በሚኒስተር መስሪያ ቤቱ የዓለም አቀፍ ቱሪዝም ፋሲሊቴሽን ዳይሬክተር አቶ ቴዎድሮስ ደርበው እንደገለፁት÷ አገልግሎት ሰጭዎቹ አስፈላጊውን ቁሳቁስ የማሟላት አቅም ባይኖራቸውም ከጤና ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት ታቅዷል።
የፕሮቶኮል መመሪያው ከአስጎብኚዎች በተጨማሪ ጎብኚዎችም አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ያዛል።
በምንይችል አዘዘው
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.