Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በአንድ የቢሮው ህንጻ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 5፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ በአንድ የቢሮው ህንጻ ላይ የደረሰው የእሳት አደጋ ምንም ጉዳት ሳያደርስ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታወቀ፡፡
የባንኩ ገዢ ዶክተር ይናገር ደሴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት የእሳት አደጋው የደረሰው ባንኩ ካሉት ሶስት የቢሮ ህንጻዎች በአንዱ ላይ ነው፡፡
እሳቱ ምንም ጉዳት ሳያደርስ በፍጥነት መቆጣጠር እንደተቻለም ዶክተር ይናገር ገልጸዋል፡፡
የእሳት አደጋው መንስኤም በመጣራት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.