Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት 330 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ ይገነባል

አዲስ አበባ ፣ ጥቅምት 9 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በተያዘው በጀት ዓመት በ1 ነጥብ 14 ቢሊየን ብር ወጪ 330 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ እንደሚገነባ የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት አስታወቀ፡፡
የክልሉ መንገድና ትራንስፓርት ቢሮ የመንገድ ኮንትራት ዘርፍ ሀላፊ አቶ ምህረት እውነቴ እንደገለፁት፥ ከሚገነባው ውስጥ 100 ኪሎ ሜትሩ በአዲስ የሚገነባ ሲሆን ቀሪው ነባር መንገድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዚህ ዓመት የሚሰሩት አዲስ መንገዶች ፍትሃዊ በሆነ መልኩ በሁሉም ዞኖች አንዳንድ የመንገድ ፕሮጀክቶች ለመስራት መታቀዱንም ተናግረዋል፡፡
እንዲሁም የመንገዱ ግንባታ አዲስ የተከፈሉ ዞኖችን ታሣቢ በማድረግ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡
በናትናኤል ጥጋቡ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.