Fana: At a Speed of Life!

በአርባምንጭ ከተማ የተገነቡ ዘመናዊ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ማዕከላት ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ጥቅምት 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአርባምንጭ ከተማ በአፍሪካ ልማት ባንክ ድጋፍ ከ33 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ ዘመናዊ የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ማዕከላት ተመረቁ፡፡

የፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃዎቹ ለቀጣይ 20 ዓመታት የከተማውን ቆሻሻ መልሶ መጠቀምና ማስወገድ የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል፡፡

የተመረቁት ልማዳዊ የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትን በተሻለ የፍሳሽ አወጋገድ ስርዓት በመተካት ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችሉ አራት የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃዎች ናቸው፡፡

ማዕከሉ የፌደራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማው ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃገር ሽማግሌዎች በተገኙበት የተመረቀ ሲሆን ÷ ለበርካታ ሰዎች የስራ ዕድል የሚፈጥር እና የአካባቢ ብክለትን የሚከላከል መሆኑ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ማዕከሉ ጊዜያዊ ስምንት ማጠራቀሚያ እና በውስጡ 80 የማጣሪያ ገንዳዎችን የያዘ የፍሳሽ ቆሻሻን መልሶ መጠቀም የሚያስችሉ  መሆናቸውን ከጋሞ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.