Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ኮሪያ መንግስት 500 ሺህ ዶላር ግምት ያለው የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ኮሪያ መንግስት 500 ሺህ ዶላር ግምት ያለው የኮቪድ-19 መከላከያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሃም ሳንግ ውክ ለጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስረክበዋል።

በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ፣ የኮሪያ ዓለም አቀፍ ጤና ደህንነት አምባሳደር ኦህ ማዩንግ ዶን፣ በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ሁንሚን ሊም እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዶክተር ሊያ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር የደቡብ ኮሪያ መንግስት ለኢትዮጵያ ላደረገው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከላከያ ቁስቁስ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ድጋፉ ኢትዮጵያ ወረርሽኙን ለመከላከል ከፍተኛ ርብርብ በምታደርግበት ወቅት የተገኘ በመሆኑ የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ትልቅ አስተዋጸኦ እንደሚያርግም ገልጸዋል።

የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ሃም ሳንግ ውክ ኢትዮጵያ በ1950ዎቹ በነበረው የኮሪያ ጦርነት ላደረገችው አስተዋጽኦ በማመስገን፤ የደቡብ ኮሪያ መንግስት ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በምትዋጋበት በዚህ ወቅት ይህንን ድጋፍ በማድረጉ ክብርና ኩራት ይሰማዋል ብለዋል።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በደቡብ ኮሪያ ባለሀብቶች እና መንግስት ከ77 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ ድጋፍ መገኘቱንም ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.