የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሀውልት ተመረቀ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 15፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ የተገነባው የአርቲስቱ ሀውልት ተመረቀ።
በሃውልቱ ምርቃት ስነ ስርአት ላይ የአርቲስቱ ቤተሰቦች፣ ጓደኞችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።
የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ታደሰ ቀነአ ሃውልቱ አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳን ለማስታወስ መገንባቱን ነው የተናገሩት፡፡
ፕሬዝዳንቱ “ለህዝብ ነጻነት ያደረገውን ተጋድሎም ያስታውሰናል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡