Fana: At a Speed of Life!

በሀዋሳ አሮጌ ገበያ የተነሳው የእሳት አደጋ በአንድ ሼድ ውስጥ የነበረ ሸቀጥን አወደመ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀዋሳ ከተማ አሮጌ ገበያ በተነሳ የእሳት አደጋ በአንድ ሼድ ውስጥ የነበረ ሸቀጥ ሙሉ በሙሉ መውደሙ ተገለፀ።

የእሳት አደጋው ሌሊት 7 ሰዓት አካባቢ ባልታወቀ ምክንያት የተነሳ ሲሆን ÷በህብረተሰቡ እንዲሁም በፀጥታ ሀይሉ ርብርብ ቃጠሎውን መቆጣጠር እንደተቻለና ወደ ሌላ ሼድ እንዳይዛመት ማድረግ መቻሉ ተነግሯል፡፡

በቃጠሎው የደረሰውን ጉዳት የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ የጎበኙ ሲሆን ከተማ አስተዳደሩ በቃጠሎው ንብረት የወደመባቸውን ነጋዴዎች በተቻለ አቅም በፍጥነት መልሶ ለማቋቋም እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው በሰው ህይወት እና በአካል ላይ ጉዳት ያልደረሰ ሲሆን የአደጋው መንስኤ እና የደረሰው የንብረት ውድመት መጠን ተጣርቶ እንደሚገለጽ ከከተማ አስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.