Fana: At a Speed of Life!

ወጣቱ በመደራጀትና የአካባቢውን ፀጋ በመጠቀም ስራ ሳይንቅ ከሰራ የለውጡ ባለቤትና ተጠቃሚ መሆን ይችላል – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 በማህበር የተደራጁ ወጣቶችን የስራ እንቅስቃሴ ጎብኝተዋል፡፡

ምክትል ከንቲባዋ ከብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለስ ዓለሙ እና ከቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መኮንን አምባዬ ጋር በመሆን በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 9 ወጣቶች በጥቃቅን እና አነስተኛ ተደራጅተው የሚያደርጉትን የስራ እንቅስቃሴ ነው የጎበኙት፡፡

በዚህ ወቅትም ወጣቶቹ በመደራጀት በወረዳው በመንገድ አካፋይ፣ በከተማ ግብርና እና በሥራ ዕድል ፈጠራ መስኮች በማከናወን ላይ ያሉትን ስራዎች አበረታችና በሃገሪቱ ከአረንጓዴው ልማት አንፃር አሻራቸውን እያስቀመጡ ነው ብለዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ አካባቢዎች ያሉ ወጣቶችም ከዚህ ልምድ በመውሰድ የአካባቢ ፀጋን በመጠቀም ወደ ልማት መሠማራት እንዳለባቸው መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተለያዩ የስራ ዘርፎች ተደራጅተው በመስራት ላይ ለሚገኙ ወጣቶችም ራዕያቸውን ለማሳካት ይረዳቸው ዘንድ የከተማ አስተዳደሩ ከአቅም ግንባታ ስልጠና ጀምሮ ሙያዊ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል፡፡

ለስራ ማስኬጃ የገንዘብ ችግር ላለባቸው ማህበራትም ብድር ይመቻችላቸዋል ነው ያሉት ምክትል ከንቲባዋ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.