በነዳጅ ምርቶች ዝውውር፣ ስርጭትና ግብይት ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 27፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በነዳጅ ምርቶች ዝውውር፣ ስርጭትና ግብይት ችግር እንዳይፈጠር ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ መሆኑን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስትሩ የመሰረታዊ ሸቀጦች አቅርቦት የዋጋ ንረት እንዳይፈጠርም እየተሰራ ነው ብሏል ።
የሚኒስቴሩ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሃገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ በተለይ በነዳጅ አቅርቦት ችግር እንዳይፈጥር ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በጊዜያዊነት የነዳጅ ማደያዎች በአዲስ አበባ ከጠዋቱ 12 ሰዓት እስከ ምሽቱ 2 ሰዓት፣ በክልል ከተሞች ደግሞ ከጠዋቱ 12 እስከ ምሽት 1 ሰዓት ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉን ኢዜአ ዘግቧል።
ዳሬክተሩ ወቅታዊ ሁኔታን ምክንያት በማድረግ በከተማዋ መሰረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች በተለይም የምግብ ሸቀጦች አቅርቦትና ስርጭት እንዳይስተጓጎል እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።