አየር ሀይሉ ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን የተመረጡ ኢላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ አድርጓል-ሜ/ጄ ይልማ
አዲስ አበባ ፣ ህዳር 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዴሪ አየር ሀይል ጠላት ሊጠቀምባቸው ያሰባቸውን የተመረጡ ኢላማዎች በመደብደብ ከጥቅም ውጭ ማድረጉን የኢፌዴሪ አየር ሀይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ አስታወቁ።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ እየሰጡ ይገኛል።
በመግለጫቸው አየር ሀይሉ ለጁንታው እስትንፋስ የነበሩ የነዳጅ ዴፖዎች ፣ የመሳሪያ ማከማቻዎች እና ሌሎች ምርጥ ኢላማዎችን ያለምንም ከልካይ ጀቶች አውድመዋቸዋል ብለዋል።
ፓይለቶች የተመረጡ ዒላማዎችን ለመደምሰስ መሣሪያ ጭነው በሚሄዱበት ወቅት ሲቪል የሚጎዳ ከመሰላቸው ሳይተኩሱ በመመለስ ነጥሎ የመምታት ስትራቴጂ እየተከተሉ እንደሚገኙም መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ጁንታው እንመታለን የሚለው ፣ እድሜውን ሲዋሽ ስለኖረና እየዋሸ ስለሚቀበር ባህሪው ነው ያሉት ሜጀር ጄኔራል ይልማ ፤ አሁንም ቡድኑ ለህግ እስኪቀርብ ድረስ አየሩ ሀይሉ ጥቃቱን እንደሚቀጥል ገልፀዋል።