Fana: At a Speed of Life!

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ ተግባራዊ የሚሆን ደንብ አፀደቀ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)የሚኒስትሮች ምክር ቤት በትግራይ ብሔራዊ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ ተግባራዊ የሚሆን ደንብ አጽድቋል።
የፌዴሬሽን ምክር ቤት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 62 (9) እና የፌዴራል መንግሥት በክልል ጣልቃ የሚገባበትን ሥርዓት ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 359/1995 አንቀፅ 14/2/ለ/ መሠረት የትግራይ ብሔራዊ ክልልን በጊዜያዊነት የሚያስተዳድር፤ ለፌዴራል መንግሥቱ ተጠሪ የሆነ ጊዜያዊ አስተዳደር እንዲቋቋም መወሰኑ ይታወቃል።

በዚህ መሠረት የሚኒስትሮች ምክር ቤት “በትግራይ ብሔራዊ ክልል የተቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ” ተግባራዊ የሚሆን ደንብ ማፅደቁን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስታውቀዋል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.