Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሽመልስ አብዲሳና ዶክተር ቀነዓ ያደታ የአሠላ ከተማ፣ አርሲ ዞንና የአሰላ ከተማ ነዋሪዎችን ድጋፍ ተረከቡ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳና የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶክተር ቀነዓ ያደታ የአሠላ ከተማ፣ አርሲ ዞንና የአሰላ ከተማ ነዋሪዎችን ድጋፍ ተረከቡ።

ከሀዲው የህወሃት አጥፊ ቡድን ያደረሰውን ጥቃት የሚያወግዝ ሰላማዊ ሠልፍ በአሰላ ከተማ ተካሂዷል።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ከአርሲ ዞንና አሰላ ከተማ የተውጣጡ ነዋሪዎች ተካፍለዋል።

መንግስት የጀመረውን ህግ የማስከበር ዘመቻ አጠናክሮ እንዲቀጥል የጠየቁት ሰልፈኞቹ፤ ለዚህም ሙሉ ድጋፍ እንዳላቸው አረጋግጠዋል።

ከጥፋት ቡድኑ ጋር በመተባበር የሀገርን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።

በገንዘብና በሚጠበቅባቸው ሁሉ ከመንግስት የህግ ማስከበርና የህልውና ዘመቻ ጎን እንደሚቆሙ የገለፁት ነዋሪዎቹ 627 የሰንጋ ድጋፍ አበርክተዋል።

በአጠቃላይም ከ24 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያላቸው ሰንጋዎች ናቸው የተበረከቱት፡፡

አፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.