Fana: At a Speed of Life!

በአዊ ብሄረሰብ ዞን ከ5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባ ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል አዊ ብሄረሰብ ዞን ከ5 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባው ትምህርት ቤት ተመርቋል፡፡

በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር በገዛራ ቀበሌ የተገነባው የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመርቆ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑ ተነግሯል።

ትምህርት ቤቱ በህብረተሰቡ ተነሳሽነት 5 ሚሊየን ብር በላይ በማሰባሰብ እና ፓርትነር ኢን ኢጁኬሽን ኢትዮጵያ ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር መገንባቱ ነው የተነገረው፡፡

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ይልቃል ከፋለ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ከ1ኛ ክፍል ጀምሮ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት በመላክ ሃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ትምህርት ቤቱ ለመማር ማስተማሩ የሚያግዙ የውስጥ ቁሳቁስ የተሟላለት ሲሆን ፕሮጀክቱ በቀጣይ አምስት ዓመት የመማር ማስተማሩን ሂደት በመደገፍ ቆይታ ያደርጋል ተብሏል፡፡

ፕሮጀክቱ ባለፉት ዓመታት በዞኑ በርካታ ትምህርት ቤቶችን ህብረተሰቡን በማስተባበር መስራቱን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.