በሀረሪ ክልል “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” መርሃ ግብር ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በሀረሪ ክልል “ለሀገር መከላከያ ክብር እቆማለሁ” በሚል መሪ ቃል ለመከላከያ ሰራዊት ልባዊ ምስጋናና ድጋፍ ስነስርዓት ተካሄዷል።
በመርሃ ግብሩ ላይ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ሚስራ አብደላ፣ ዋና አፈ ጉባኤ አዲስአለም በዛብህ፣ አቶ ኻሊድ አልዋንን ጨምሮ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የምስራቅ እዝ መከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊስ አመራሮች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ ለአንድ ደቂቃ ቀኝ እጃቸውን ግራ ደረታቸው ላይ በማድረግ ለመከላከያ ሠራዊት ያላቸውን ክብር ገልፀዋል።
እንዲሁም ለአንድ ደቂቃ በማጨብጨብ ለመከላከያ ሰራዊቱ ድጋፋቸውን መግለፃቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በተጨማሪም በህግ ማስከበር ትግል ህይወታቸው ላለፈ የመከላከያ ሰራዊት አባላትና በጁንታው የጥፋት ሴራ ህይወታቸው ላጡ ንፁሃን ዜጎች የአንድ ደቂቃ የህሊና ፀሎት ተደርጓል፡፡