Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 533 የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ13 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 9፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 4 ሺህ 871 የላቦራቶሪ ምርመራ 533 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 103 ሺህ 928 ደርሷል።
በሌላ በኩል የዛሬውን ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 64 ሺህ 593 ሆኗል።
እንዲሁም የ13 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 601 መድረሱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.