Fana: At a Speed of Life!

ባለፉት 24 ሰዓታት 499 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው የ6 ሰዎች ህይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 5 ሺህ 201 የላቦራቶሪ ምርመራ 499 ሰዎች ኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህም በኢትዮጵያ በአጠቃላይ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 104 ሺህ 427 ደርሷል።
በሌላም በኩል በዛሬው እለት ያገገሙትን 390 ሰዎችን ጨምሮ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 64 ሺህ 983 ሆኗል።
እንዲሁም የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉ መረጋገጡን ተከትሎ በበሽታው የሞቱ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 607 መድረሱን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.