Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ አቁሟል በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሰሜን የሀገሪቱ ክፍል በወሰደችው የህግ ማስከበር እርምጃ ምክንያት የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮጵያ የሚሰጠውን ድጋፍ አቁሟል በሚል የተሰራጨው መረጃ የተሳሳተ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለፁ፡፡
ከፈረንጆቹ 2014 ጀምሮ እስከ 2020 ድረስ የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያ ለተለያዩ ዘርፎች ማስፈፀሚያ የሚውል ከለገሰው 815 ሚሊየን ዩሮ ውስጥ 95 በመቶ የሚሆነውን ኢትዮጵያ በአግባቡ መጠቀሟን ቃል አቀባዩ አንስተዋል፡፡
ቀሪውን የገንዘብ ድጋፍ ለመልቀቅ ደግሞ በሀገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢ በተፈፀመው የህግ ማስከበር እርምጃ ላይ መሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎች እንዳስቀመጠ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል፡፡
በአውሮፓ ህብረት እና በአፋሪካ ሀገራት መካከል በነበረው የቆየ ሰምምነት መሰረት ህብረቱ በአካባቢው የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲገባ፣ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ጉዳዩን እንዲከታተሉ፣ ጉዳት የደረሰባቸው የመሰረተ ልማት ተቋማት እንዲሟሉ እና ጉዳዩ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀምጦ እንደነበር አምባሳደር ዲና ጠቁመዋል፡፡
ይህንን ቅድመ ሁኔታ በተሳሳተ መንገድ ወስዶ ህብረቱ ለኢትዮጵያ ድጋፍ አቁሟል በሚል የተሰራጨው ዘገባ መሰረተ ቢስ መሆኑንም ነው ቃል አቀባዩ የተናገሩት፡፡
ከህግ ማስከበር እርምጃው ጋር ተያይዞ እስካሁን የተፈጠረ ዓለም አቀፋዊ እንከን የለም ያሉት አምባሳደር ዲና የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ የውስጥ ሰላም ለቀጠናው መረጋጋት ማዕከል መሆኑን እና ኢትዮጵያ የአህጉሩ የሰላም ተምሳሌት መሆኗን ተቀብለዋል ማለታቸውን አብመድ ዘግቧል፡፡
ብሔራዊ ጥቅምን በጋራ ለማስከበር እና በውጭ ያለን ተሰሚነት አጠናክሮ ለማስቀጠል የውስጥ ሰላም ወሳኝ እንደሆነ አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።
በሀገር ውስጥ የህግ የበላይነትን እያስከበርን በውጭው ዓለም እና በአህጉሪቷ ያለንን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን ነው ያሉት፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.