Fana: At a Speed of Life!

ጊዜያቸው ያላለፈባቸውን የሬዲዮ መገናኛዎች ኮሚቴ አቋቁመው ለህወሃት የፀረ-ሰላም ቡድን የላኩ መኮንኖች ፍርድ ቤት ቀረቡ

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሰራዊት ኮሙዩኒኬሽን ኃላፊ ሜጀር ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴን ጨምሮ 7 የመከላከያ መኮንኖች ችሎት ቀርበዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ ሀገርን በመክዳት ወንጀልና ህገመንግስትና ህገመንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለመናድ ማሰብ ወንጀል በቁጥጥር ስር ውለው በፌዴራል ፖሊስ ኮሚሸን ወንጀል ምርመራ ዘርፍ በምርመራ ላይ የሚገኙ ሲሆን÷ተጠርጣሪዎቹ ዛሬ በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ቀርበው ጉዳያቸው ታይቷል፡፡
መርማሪ ፖሊስ ከዚህ በፊት ከተቀበለው የ14 ሰዎችን የምስክር ቃል በተጨማሪ የስምንት ሰዎቸን የምስክርነት ቃል ተቀብሎ ከመዝገቡ ጋር ማያያዙን ለችሎቱ ገልጻል።
የሰሜን እዝ የመገናኛ ኔትወርክ አቋርጠው ከሌሎች ግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በእዙ ጥቃት እንዲደርስ ማድረጋቸውን በሰውና በቴክኒክ ማስረጃ ማረጋገጡን መርማሪ ፖሊስ ገልጿል።
በዚህም ተጠረጣሪዎቹ በስራ ላይ በነበሩበት ወቅት ብሄርን ማእከል ያደረጉ ግጭቶች ሲነሱ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ ሲኖርባቸው በቸልተኝነት በማለፍ ግጭቱ እንዲባባስ ሲያደርጉ እንደነበር መረጃ አግኝቻለው ብሏል።
በተጨማሪም ተጠርጣሪዎቹ የአገልግሎት ጊዜያቸው ያላለፈባቸውን የሬዲዮ መገናኛ መሳሪያዎች ኮሚቴ አቋቁመው ለህወሓት የፀረ-ሰላም ቡድን መገልገያነት እንዲውሉ ወደ ትግራይ መላካቸውን ፖሊስ አስረድቷል፡፡
ከዚያም ባለፈ ተጠርጣሪዎቹ በስራ ክፍላቸው ላይ ሆነው የትግራይ ተወላጆችን እየመለመሉ ወደ ትግራይ ልዩ ሃይል ሲልኩ እንደነበር በሰበሰብኩት ማስረጃ አረጋገጫለው ያለው መርማሪ ፖሊስ ÷በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ማድረጋቸውን በርከታ መረጃ ሰብስበናልም ነው ያለው።
ቀረኝ ባላቸው የምርመራ ስራዎች ማለትም በተጠርጣሪዎች እጅ ላይ የተገኘ ኤሌክትሮኒክስ መሳሪያን ለብሄራዊ መረጃ ደህንነት ለምርመራ ልኮ ውጤቱን እየተጠባበቀ መሆኑን ጠቅሷል።
በደረሰው ልክ የተጎጂዎችን ቃል ለመቀበል ተገለው በጅምላ የተቀበሩ በርካታ ዜጎችን አስከሬን ፣ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጂዎች እንዲሁም የወደመውን የህዝብና የመንግስት ንብረት መጠን አጣርቶ ውጤቱን ለማቀረብና መለየት፣ በተለያዩ አካባቢዎች ለመርመራ የተላኩ የመርመራ ቡድኖች የተሰሩ ስራዎችን ማስመጣት፣ከተለያዩ የመንግስት ተቋማትና ባንኮች መረጃ የማስመጣት ስራ እንደሚቀረው ጠቅሷል።
ተጠርጣሪዎችም በጠበቃቸው ተወክለው ችሎት ተገኝተው መቃወሚያዎችን አሰምተዋል፡፡

በተለይም ምርመራው በጅምላ ነው እየተከናወነ ያለው በተናጠል ተሳተፏቸው አልተገለጸም ከማን ጋር ማን የሚለው ተሳተፎ  ባልተገጸበት ሁኔታ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብነት የለውም ብለዋል።

ተጠርጣሪዎቹ የመገናኛ ሬዲዮ ኔትወርክ የማቋረጥ ስልጣን የላቸውም  ከወንጀሉ ጋር ግንኙነት የላቸውም በመታሰራቸው ቤተሰቦቻቸው  ተቸግረዋል ፍርድቤቱ ይህን ተረድቶ በዋስ  ወጥተው  በቤታቸው ሆነው ምርመራው ይቀጥል  ከሃገር እንዳይወጡ እግድ ሊጣል ይቻላል ሲሉም ጠበቆቻቸው የዋስትና ጥያቄ አንስተዋል።

መርማሪ ፖሊስም ከሃገር እንዳይወጡ ታገደውም በዋስ ቢወጡ በመከላከያ ስራ ላይ ያሉ በተለያየ  አጋጣሚ የሚያወቋቸው ስላሉ  ምስክርም ሆነ ማስረጃ ሊያሸሹ ይችላሉ ሲል ተቃውሟል።

1ኛ ተጠርጣሪ ሜጀር ጄኔራለ ገብረመድህን የአዲስ አባባ ዩኒቨርስቲ የማስተርስ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ለመከታተለ ፎርም እንዲሞሉ ይፈቀድ ሲሉ ያመለከቱ ሲሆን÷ 5ኛ ተጠርጣሪ ብርጋዴል ጄኔራለ ፈስሃ ገ/ስላሴ የልብና የደም መርጋት ህመምተኛ መሆናቸወን ጠቅሰው የፌዴራል ፖሊስ ወስዶ በፖሊስ ሆስፒታል እንዳሳከማቸው ገልጸው ነገር ግን አጠቃላይ አልትራ ሳወንድ ምርመራ ለማድረግ ወደ ህዳሴ እንዲላኩ ጠይቀዋል ፍርድቤቱም የሪፈር ትዛዝ በሌለበት ሁኔታ እንዴት እኔ ሪፈር ብዬ ፈቅዳለው ሲል ምላሽ ሰጥቷል።

የተጠርጣሪዎቹ የልጆቻቸው የትምህርት ቤት መጠቀሚያ የሚውለው ላፕቶፖቻቸው ለምርመራ ተውስዷል ቢመለስ የሚል ጥያቄም አንስተዋል።

ችሎቱም መዝገቡን መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለታሳስ 15 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።

ችሎቱም መዝገቡን መርምሮ ትዛዝ ለመስጠት ለታሳስ 15 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰቷል።
በታሪክ አዱኛ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.