Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ሳተላይት አመጠቀች

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 13፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ኢቲ ስማርት አር ኤስ ኤስ ( ET-Smart-RSS )የተባለች ሳተላይት ማምጠቋን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት በፌስ ቡክ ገጹ አስታውቋል።
ኢትዮጵያ ባለፈው ዓመት ETRSS-1 የተባለች የመጀመሪያዋን የመሬት ምልከታ ሳተላይት ታኅሣሥ ወር 2012 ዓ.ም ማምጠቋ ይታወሳል።
ባለፈው አመት የመጠቀችው “ETRSS-1” የሚል ስያሜ የተሰጣት ምድርን እየቃኘች ፎቶ እየመዘገበች መረጃ የምትሰበስበው ሳተላይት በሀገራችን የዕድገት ጉዞ ላይ ቁልፍ ሚና እንደሚኖራት መነገሩ ይታወሳል።
መረጃ መላክ የጀመረችው ይች ሳተላይት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቆጣጠር፣ ከግብርና ጋር የተያያዙ ጥናት እና ምርምሮችን ለመሥራት እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ የመሠረተ ልማት ተግባራትን በማከናወን ላይ ትገኛለች።
አሁን የመጠቀችው ET-Smart-RSSም ተግባር የመሬት ምልከታ ሆኖ የምስል ጥራቷ ግን ከበፊቱ በእጅጉ የተሻለ መሆኑን የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይስን እና ቴክኖሎጂ ኢስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል።
ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ETRSS-1 ማይክሮ ሳተላይት መሆኗን ጠቁመው÷ ET-Smart-RSS ደግሞ ናኖ ሳተላይት እንደሆነች እና የዘመኑን የረቀቀ ቴክኖሎጂ የያዘች መሆኗን ተናግረዋል።
ሁለቱ ሳተላይቶች አንድ ላይ ሲጣመሩ የተሻለ የመሬት ምልከታ አገልግሎት ማግኘት እንደሚቻልም አመልክተው፣ ኢንቲትዩቱ የሁለቱን ምስሎች በማቀናጀት የሚቀበል መሆኑን ተናግረዋል።
በአሁኑ ጊዜ ብዙ ሳተላይቶች የተለያዩ ቦታ ሆነው ሰፊ ቦታ በመሸፈን በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ምስል ማግኘት እንደሚቻልም ተናገረዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.