በወላይታ ሶዶ ከተማ በመርካቶ ገበያ ማዕከል ሰሞኑን በደረሰ የእሳት አደጋ ከ1 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጣ ንብረት መውደሙ ተገለጸ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው በአደጋው ተጎጂ ከሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያዩ፡፡
የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ዶክተር እንድርያስ በዕለቱ የተነሳው የእሳት አደጋ በርካቶችን መና ያስቀረ እንደነበር ጠቁመው ከቀን ገቢ መተዳደሪያ እስከ ከፍተኛ የንግዱ ማህበረሰብ የአደጋው ሰለባ ሆነዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በገበያ ማዕከሉ በደረሰ አደጋ 1 ቢሊየን 57 ሚሊየን 670 ሺህ ብር የሚያወጣ ንብረት የወደመ ሲሆን 5 ሺህ 378 የህብረተሰብ ክፍሎች ደግሞ ተጎጂ ሆነዋል ነው ያሉት፡፡
አደጋው ከደረሰበት ጊዜ ጀምሮ የሲዳማ ክልል አጎራባች ዞኖች ባለሀብቶች እንዲሁም ህብረተሰቡ ጉዳቱ የከፋ እንዳይሆን ላደረጉት ድጋፍ አመስግነው የአደጋው ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት ባለሀብቶች እና ህብረተሰቡ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የደቡብ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ እርስቱ ይርዳው ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
ተጎጂዎችን ለማቋቋም በተዘጋጀው የባንክ አካውንት የክልሉ መንግሥት 10 ሚሊየን ብር ድጋፍ እንደሚያደርግም ነው የተናገሩት፡፡
የክልሉ መንግሥት አስቸኳይ የእለት ደራሽ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት መዘጋጀቱን የተናገሩት አቶ እርስቱ አካባቢው በዘላቂነት መልማት እንዲችል እና ለአደጋ ተጋላጭ እንዳይሆን እንደሚሰራም አንስተዋል፡፡
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ደግሞ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ መጠየቃቸውን ከደቡብ ክልል መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!