የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በዜጎች ላይ በደረሰው ጥቃት የተሰማውን ሀዘን ገለፀ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 16 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በንፁሀን ዜጎች ላይ በደረሰው ኢ- ሰብአዊ ድርጊት የተሰማውን ሃዘን ገልጿል፡፡
ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በሰላም ተንቀሳቅሰው መኖር የሚችሉበትን ሰብአዊ መብታቸውን የገረሰሰው ይህ አሰቃቂ ጥቃት እጅጉን አሳዛኝ እና ለዘመናት አብሮ ተቻችሎ እና ተፈቃቅሮ የኖረ ህብረተሰብ መሀል ይከሰታል ተብሎ የሚጠበቅ አይደለም ብሏል ክልሉ።
የዚህ አይነቱና መሰል ኢ-ሰብአዊ ድርጊት በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል እንዳይደገም ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት መንግስትና ህዝብ በጋራ በመሆን በተለይም የየአካበቢውን ነባር የእርቅ፣ የፍቅር እና የመቻቻል እሴቶች በማዳበር ባህላዊ አደረጃጀቶችን በጥናት በመደገፍ ቀጣይነት ያለው ስራ መስራት ይገባልም ነው ያለው።
ጥፋቶች ሳይከሰቱ በፊት አዝማሚያዎችን በመከታተል እና ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ ትንታኔ በመስጠት ቅድመ መከላከል ስራ ላይ በተለየ መልኩ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያለው በሃዘን መግለጫው።
በተለይም ህዝቡን ዋና የሰላሙ ዘብ፣ ዋና ጠባቂ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ህዝቡ በንቃት አካባቢውን እንዲጠብቅ እና የሰላም ተምሳሌትነቱን እንዲያስቀጥል ከሚመለከታቸው የመንግስት ተቋማት ጋር የማስተባበር እና የመምራት ስራ ይጠበቃል።
በደረሰው ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ፣ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው እና ንብረታቸው ለወደመባቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን መፅናናትን እንመኛለን ብሏል የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!