ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመንገድ ፣ የወደብ አገልግሎቶችን እና የመኪና ማቆሚያ ጣቢያዎችን ይዘት ለማሻሻል ተስማሙ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጅቡቲ የመንገድ፣ የወደብ አገልግሎቶችን እና የመኪና ማቆሚያ ጣቢያዎችን ይዘት ለማሻሻል ተስማምተዋል፡፡
በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ ከጅቡቲ ወደቦች ዓለም አቀፍ ነፃ የንግድ ቀጠና ሊቀመንበር አቡበከር ዑመር ሀዲ ጋር ውይይት አካሂደዋል ፡፡
በዚሁ ወቅት አምባሳደር ብርሀኑ÷ ለሁለቱ ሃገራት ኢኮኖሚያዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክተው የዲኪል-ዳጉሩ መንገድ በፍጥነት መጠናቀቅ እንዳለበት አውስተዋል።
በዚህ ወቅት ሁለቱ ወገኖች ቀሪውን 80 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመጀመር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተስማምተዋል ፡፡
ከዚህ ባለፈም የዶራሌ ሁለገብ ወደብን እና የጅቡቲ ኮንቴነር ተርሚናል ከኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ሀዲድ ጋር በማገናኘት የወደብ አገልግሎቶችን አቅም ማሻሻል በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ሃሳብ ተለዋውጠዋል፡፡
በተጨማሪም ከጅቡቲ በኩል በሆራይዘን ነዳጅ ማደያ እና ከኢትዮጵያ በኩል ወደ ኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መስመር በአዋሽ የሚገኘውን የነዳጅ ማከማቻ ግንኙነት ለማቋቋም ተስማምተዋል ፡፡
ይህ የነዳጅ ጭነት ቀልጣፋ ፍሰት እና ህገ-ወጥ የነዳጅ ዘይት ግብይትን ለመከላከል ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል ፡፡
የጅቡቲ ወደብ እና የነፃ ቀጠና ባለስልጣን የኢትዮጵያ መንግስት ከደረቅ ወደብ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ አስተዳደራዊ አሰራር ለማስቀመጥ የነዳጅ ተርሚናል የባለቤትነት መብት ማረጋገጫ ሰነድ ለማግኘት ያቀረበውን ጥያቄ ተቀብሏል፡፡
ሊቀመንበሩ የባለቤትነት ማረጋገጫ ወረቀቱን ለኢትዮጵያ በፍጥነት ለመስጠት ቃል መግባታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!