በምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ በደረሰ የእሳት አደጋ 586 ሚሊየን 142 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወደመ
አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል ምዕራብ ኦሞ ዞን ቤሮ ወረዳ ሾላ ቀበሌ በደረሰ የእሳት አደጋ 586 ሚሊየን 142 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወደመ ፡፡
አደጋው የደረሰው ትናንት አመሻሽ ላይ ሲሆን በአደጋው 1 ሺህ 840 መኖሪያ ቤቶች፣ 547 የንግድ ቤቶች፣ 37 የወርቅ ማህበራት፣ 109 የወርቅ ማሽን መውደማቸውን የቤሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ዶንቴስ ባይኬስ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል፡፡
የአደጋው መነሻ ከአንድ ጸጉር ቤት የተነሳ እሳት መሆኑን አስተዳዳሪው ገልፀዋል፡፡
በዘረያዕቆብ ያዕቆብ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል www.youtube.com/fanatelevision ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!