የተማሪዎችን የፈጠራ ውጤቶች በአግባቡ መምራት የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ ተዘጋጀ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 23፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በምህንድስና፣ በጥበብና ሂሳብ ዘርፍ የሚቀርቡ የተማሪዎችን የፈጠራ ስራዎች ከዚህ በፊት ከነበረው አሰራር ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ረቂቅ መመሪያ ማዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡
መመሪያው ተወዳዳሪዎች በተቀመጠላቸው የመወዳደሪያ መስፈርት መሰረት የፈጠራ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡና አሸናፊዎች በማያሻማ መልኩ ተለይተው ተገቢውን ማበረታቻ እንዲያገኙ የሚያግዝ መሆኑ ነው የተገለፀው፡፡
ከሁሉም ክልሎች የተውጣጡ ባለሙያዎች በአውደ ጥናቱ ላይ በመሳተፍ ለረቂቅ መመሪያው ግብአት የሚሆኑ ሃሳቦችን አንስተው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በአውደ ጥናቱ የተሳተፉ ባለሙያዎችም መመሪያው በውድድር ሂደት ሊነሱ የሚችሉ ቅሬታዎችን ለመቀነስ ጉልህ ሚና እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
ከአዲሱ የትምህርት አደረጃጀትና ሥርዓት ጋር የተጣጣመ እንዲሆንም መመሪያው በትኩረት መሰራት እንዳለበት መገለጹን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!