የብሪታኒያ ፍርድ ቤት የዊኪሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጄ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዳይሰጥ ወሰነ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የብሪታኒያ ፍርድ ቤት የዊኪሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጄ ለአሜሪካ ተላልፎ እንዳይሰጥ ውሳኔ አሳለፈ።
አሳንጄ በስዊድን ወሲባዊ ጥቃት ፈፅመሃል በሚል እንግሊዝ በሚገኘው የኢኳዶር ኤምባሲ በጥገኝነት ቆይቶ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በፊት ለፖሊስ ተላልፎ መሰጠቱ የሚታወስ ነው።
ኢኳዶር ጁሊያን አሳንጄን ለብሪታኒያ ፖሊስ አሳልፋ ከሰጠች በኋላ ለአሜሪካ ተላልፎ ይሰጥ አይሰጥ በሚለው ጉዳይ ላይ የፍርድ ሂደቱን እየተከታተለ ቆይቷል።
ጁሊያን አሳንጄ እራሱን ሊያጠፋ ይችላል የሚል ስጋት ስለገባቸው ዳኛው ለአሜሪካ አሳልፎ ላለመስጠት መወሰናቸውን ተናግረዋል፡፡
አሳንጄ ኮምፒውተሮችን ለመጥለፍ እና ብሄራዊ የመከላከያ መረጃ ለማግኘት አሲሯል በሚል በአሜሪካ 18 ክሶች እንደቀረቡበት የሚታወስ ነው።
የቀረበበትን ክስ ውድቅ ያደረገው አሳንጄ የማንኛውንም አካል ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ስራ መስራቱን የሚያመለክት ማስረጃ የለም ብሏል።
ምንጭ፦ ስካይ ኒውስ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!