አቶ አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ የስራ ሀላፊዎች ሹመት ሰጡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ለተለያዩ የስራ ሀላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
1. አቶ ጎሹ እንዳላማው የርዕሰ መስተዳድሩ የህዝብ ግንኙነት አማካሪ
2. አቶ ደሳለኝ አስራደ የርዕሰ መስተዳድሩ ልዩ አማካሪ
3. አቶ መስፍን አበጀ የርዕሰ መስተዳድሩ የመሰረተ ልማት አማካሪ
እንዲሁም ወይዘሮ ከድጃ ሁሴን በምክትል ቢሮ ሃላፊ ማእረግ የአደረጃጀት ምክትል ዘርፍ አማካሪ ሆነው መሾማቸውን ከአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!