Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ፓርቲው 10 ሚሊየን የሚጠጉ አባላትና አመራር እንዳሉት አስታወቀ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ብልፅግና ፓርቲ 10 ሚሊየን የሚጠጉ አባላት እና አመራር በመላ ሀገሪቱ እንዳሉት አስታወቀ፡፡

ኮሚሽኑ የ2013 በጀት ዓመት የ6 ወራት የሥራ አፈፃፀሙን እየገመገመ ሲሆን ፓርቲው በአሁኑ ሰዓት 9 ሚሊየን 941 ሺህ 467 አባላት እና አመራሮች በመላ ሀገሪቱ እንዳሉት ገልጿል፡፡

እነዚህ አባላት በዳታ ቤዝ መመዝገብ እንዳለባቸው ነው የገለፀው፡፡

ለፓርቲው ውስጠ ዴሞክራሲ መጠናከር ኮሚሽኑ የበኩሉን እንደሚወጣ የፓርቲው ማዕከላዊ ቁጥጥርና ኢንስፔክሽን ኮሚሽን ኮሚሽነር ኢንጂነር አወቀ ሃይለማርያም ገልፀዋል፡፡

ከዚህ በፊት በአራቱ ክልሎች ተወስኖ የነበረው ስራ በሁሉም ክልሎች በአዲስ መልክ መደራጀቱ ሁሉም ክልሎች የሀሳብና የተግባር አንድነት ወጥ ሆኖ እንዲቀጥል ዕድል የፈጠረ ነውም ብለዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.