Fana: At a Speed of Life!

ተጨማሪ 555 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ሲገኝባቸው 507 ሰዎች ሰዎች ደግሞ አገግመዋል

አዲስ አበባ ፣ ጥር 14 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት 24 ሰአታት ለ4 ሺህ 951 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 555 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው እለታዊ መግለጫ 507 ሰዎች ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን ይህን ተከትሎም 118 ሺህ 513 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።

ከዚህ ባለፈም ባለፉት 24 ሰአታት የሶስት ሰዎች ህይወት በቫይረሱ ሳቢያ ያለፈ ሲሆን እስካሁን 2 ሺህ 60 ሰዎች በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት ተዳርገዋል።

227 ሰዎች ደግሞ አሁን በጽኑ ህክምና ላይ ይገኛሉ።

እስከዛሬ በኢትዮጵያ ለ1 ሚሊየን 908 ሺህ 533 ሰዎች የላቦራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን፥ 132 ሺህ 881 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.