ሱዳን በአባይ ወንዝ ላይ 18 ኪሎ ሜትር ቦይ በመስራት 170 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ልታለማ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን በአባይ ወንዝ ላይ 18 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ቦይ በመስራት 170 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ልታለማ ነው።
በሰሜን ምስራቅ ሱዳን ኑቢያ በርሃ እጅግ ሰፊ በርሃማን ስፍራ ዳል ግሩፕ የተሰኘ ድርጅት በመስኖ ለማልማት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ፋይናሻል ታይምስ ዘግቧል።
የዳል ግሩፕ ሊቀመንበር ኦስማን ዳውድ እንደሚታወቀው አካባቢው በርሃ ነው ነግር ግን አረንጓዴነት በመቀየር ላይ እንገኛለን ብለዋል።
የአባይ ወንዝ አለን፣ ሌሎች በርካታ ወንዞች አሉን ፣ የዝናብ ውሃ በተመሳሳይ አለን ያሉት ሊቀመንበርሩ በዓለም ላይ ሜዳማ ሀገር አለን ብለዋል።
አቡ ሃማድ በተሰኘው የሱዳን አካባቢ በ225 ሚሊየን ዶላር ወጪ ድርጅቱ ከዱባዩ ሮያል ግሩፕ ጋር በጋራ በመሆን የመስኖ ልማቱን እንደሚሰራ ተነግሯል።
ከአባይ ወንዝ 10 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ለሚለማው እርሻ 18 ኪሎ ሜትር ቦይ በመስራት ከአባይ ወንዝ ውሃ እንደሚሳብ ነው ።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!