Fana: At a Speed of Life!

በአለም በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሚሊየን አለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በአለም ዙሪያ በኮሮና ቫይረስ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2 ሚሊየን መሻገሩን መረጃዎች ያመላክታሉ።

በአለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከ2 ሚሊየን 184 ሺህ በላይ ደርሷል።

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም ከ101 ሚሊየን 441 ሺህ በላይ መሆኑን ነው መረጃው የሚጠቁመው፡፡

በተለይም በቫይረሱ ክፉኛ የተጎዱት ሰሜን እና ደቡብ አሜሪካ በቫይረሱ ሳቢያ ለህልፈት የተዳረጉ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊየን ያለፈ ሲሆን÷ ከ44 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

አሜሪካ፣ ህንድ፣ ብራዚል፣ ሩሲያ እና ብሪታንያ ቫይረሱ ከጸናባቸው አገራት መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

በአንጻሩ በአለም ከ73 ሚሊየን 325 ሺህ በላይ ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

ምንጭ፡- ሲጂቲኤን እና ዎርልድ ኦ ሜትር

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.