በአልባሳትና በቆዳ ውጤቶች ላይ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች በሱዳን የሚገኝ ግዙፍ ፋብሪካን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ)በአልባሳትና በቆዳ ውጤቶች ላይ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች በሱዳን የሚገኝ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ፋብሪካን ጎበኙ፡፡
በ38ኛው የካርቱም አለም አቀፍ የንግድ ኤግዚብሽን ላይ በቆዳ ውጤቶችና አልባሳት ዘርፍ የተሰማሩ የኢትዮጵያ ኩባንያዎች አሎማር ግሩፕ የተባለ በሱዳን ሶባ አካባቢ የሚገኝ ትልቅ የጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ኩባንያን ጎብኝተዋል።
ኩባንያው ጥሬ እቃ ከህንድና ከሌሎች አገራት በማስመጣት የሚጠቀም ሲሆን ከሽመና ጀምሮ አስከ ጨርቃጨርቅ እና አልባሳት ማምረት ድረስ ያሉ ሂደቶችንና ይሰራል፡፡
ለዚሁ ሥራ የሚውሉ የተለያዩ ዘመናዊ ማሽኖችን በመጎብኘት ጠቃሚ ልምዶችን ማግኘት መቻሉን በሱዳን ከኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላታል፡፡
በቀጣይ በጋራ መስራት ስሚቻልበት ሁኔታም ውይይት ተካሂዷል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!