Fana: At a Speed of Life!

ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ የአማራ ክልል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችን ጉበኙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ)የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ የአማራ ክልል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችን ጉበኙ፡፡
ፕሬዚዳንቷ በጉበኝታቸው ወቅት የአማራ ክልል ጠቅላይ እና ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችን የክስ መዝገቦች ውሳኔ አሰጣጥ እና የችሎት የመረጃ አያያዝ ተመልክተዋል፡፡
ከጉብኝት በኋላ ከዳኞች እና ከማኔጅመንት አባላት ጋር ውይይ አካሄደዋል፡፡
በክልሉ 209 ፍርድ ቤቶች ያሉ ሲሆን በነዚህ ተቋማት ለአገልግሎት አሰጣጥ የሚሆን የበጀት እና የግብአት እጥረት መኖሩ ተነግሯል፡፡
ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ የግብአት ችግሮችን ለመፍታት የፌዴራል መንግስት ከክልሉ መንግስት ጋር በቅንጅት ይሰራል ብለዋል፡፡
በናትናኤል ጥጋቡ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.