በትግራይ ክልል እየተደረገ የሚገኘውን ሰብዓዊ ድጋፍ ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚጥሩ አካላት እንዳሉ ተገለፀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጨምሮ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አትላንቲክ ካውንስል የአፍሪካ ማዕከል ባዘጋጀው የበይነ መረብ ውይይት ላይ አለም አቀፉ ማህበረሰቡን ባሳሰቡ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በዚህ ውይይት ላይ የተወሰኑ የአሜሪካ የኮንገረስ እና የጆ ባይደን አስተዳደር አባለት ተሳታፊ ሆነዋል።
እንዲሁም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሬድዋን ሁሴን እና የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ተስፋሁን ጎበዛይ ተሳትፈዋል።
በማብራሪያቸውም በትግራይ ክልል የተካሄደውን ህግን የማስከበር እርምጃ ተከትሎ የትግራይ ክልል ወደ መደበኛነት እየተመለሰ መሆኑን ተናግረዋል።
የህዝቡን ማህበራዊ እና አኮኖሚያ ልማድ የመመለስ እና መሰረተ ልማቶችን መልሶ የመገንባት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ በማብራሪያው ላይ ተጠቅሷል።
በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን ዜጎች ትክክለኛውን ቁጥር ለተሳታፊዎቹ የቀረበ ሲሆን በተለያዩ አካላት ተጋኖ እንደሚቀርብ ተነግሯል።
በክልሉ በሰፍትኔት ፕሮግራም ታቅፈው የነበሩ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች እንደነበሩ እና አሁን ላይ ከእነዚህ ውስጥ 700 ሺህ ዜጎች ህግን የማስከበር እርምጃው ተከትሎ ለችግር መዳረጋቸው ተጠቁሟል።
በክልሉ በሚገኙ 92 የማከፋፈያ ማዕከላትን በመጠቀምም ለ1 ሚሊየን 46 ሺህ ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ እንደደረሳቸው ተገልጿል።
የኢትዮጵያ መንግስት ለትግራይ ህዝብ የሰብዓዊ ድጋፎችን እያቀረበ እንደሚገኝ እና በክልሉ መንግስት ባስቀመጠው መመሪያ መሰረት ጉብኝት ማድረግ ለሚፈልጉ ዝግጅት መደረጉም ለተሳታፊዎቹ ተነግሯል።
የመንግስት የስራ ሃላፊዎቹ የተራድኦ ድርጅቶች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ጉዳዩን ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚያደርጉትን ጥረት ወቅሰዋል።
የኤርትራ ስደተኞችን በተመለከተም በማይ አይኒ እና አዲ ሃሩሽ መጠለያ ጣቢያዎች ድጋፍ የተደረገላቸው መሆኑ ያነሱት የስራ ሃላፊዎቹ በሀገር ውስጥ እና በዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ በመንግስት የቀረበው ሀሰተኛ ወቀሳ እንዳሳዘናቸው ገልፀዋል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!