Fana: At a Speed of Life!

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በሲቲ ዞን ሺኒሌ ወረዳ የተገነባውን ዘመናዊ የተሽከርካሪዎች መናኸሪያን መርቀው ከፈቱ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2013 (ኤፍቢሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ በሲቲ ዞን ሺኒሌ ወረዳ የተገነባውን ዘመናዊ የተሽከርካሪዎች መናኸሪያን መርቀው ከፈቱ፡፡

በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ፕሮጀክቶችን በተያዘላቸው ጊዜ ውስጥ የማጠናቀቅ ትልቅ እመርታ እየታየ መሆኑን ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የገለጹት፡፡

ከ15 ሚልየን ብር በላይ ወጪ የተገነባው ይህ ዘመናዊ መናኸሪያ ከ12 ሺህ ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ነው ተብሏል፡፡

በቀን ለ7 ሺህ ዜጎች አገልግሎት እና መስተንግዶ መስጠት እንደሚችል የሶማሌ ክልል ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሮብሌ አዋሌ ገልፀዋል፡፡

የመናኸሪያው በዚያ አከባቢ መገንባት ለአከባቢው ማህበረሰብ የስራ ዕድል ከመፍጠሩም በላይ አከባቢውን ወደ ከተማ ይቀይራል ነው ያሉት፡፡

ይህ ዘመናዊ መናኸሪያ የሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን እና ፋፈን ዞን ወረዳዎች የሚያስተሳስር ሲሆን ሀገሪቷንም ከጂቡቲ ጋር ያስተሳስስራል።

በሽኒሌ ወረዳ የተገነባው ዘመናዊ የተሽከርካሪዎች መናኸሪያ በድሬደዋ-አይሻአ-ደወንሌ የክፍያ መንገድ በቅርብ ርቀት ላይ የተገነባ ሲሆን ከ200 በላይ ተሽከርካሪዎችን በቀን የማስተናገድ አቅም እንዳለው ከክልሉ ብዙኀን መገናኛ ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.