Fana: At a Speed of Life!

ከ1 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የሚገነባው የጨጎማ ጋሸና መንገድ ግንባታ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ወሎ ዞን የኩርባ መገንጠያ የሆነው ጨጎማ – ጋሸና የአስፓልት ኮንክሪት የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት በይፋ ተጀመረ።

44 ነጥብ 7 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው ጨጎማ – ጋሸና የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ከዚህ ቀደም በጠጠር ደረጃ የተገነባ ነበር፡፡

መንገዱ ካለው ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳ አንጻርም በአስፓልት ኮንክሪት እንዲገነባ መወሰኑ ተነግሯል።

በግንባታ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ከፍተኛ የፌደራልና የክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡

የፕሮጀክቱ ግንባታውን በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ የተያዘ ሲሆን፥ ዮቴክ ኮንስትራክሽን ግንባታውን ያከናውነዋል ተብሏል፡፡

ለግንባታውም 1 ቢሊየን 434 ሚሊየን 519 ሺህ ብር ተመድቦለታል፡፡

በተስፋዬ ከበደ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.