Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል ተቋርጦ የነበረውን የትራንስፖርት አገልግሎት በማስጀመር የፌዴራል ፖሊስ አባላት ትልቁን ድርሻ እንደተወጡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን የትራንስፖርት አገልግሎት በማስጀመር የፌዴራል ፖሊስ አባላት ትልቁን ድርሻ እንደተወጡ የመቀሌ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ከበደ አሰፋ ችግሩን ለመቅረፍ መንግስት ሁሉም አገልግሎቶች ወደቀድሞ ስራቸው እንዲመለሱ ባስተላለፈው ጥሪ መሰረት የተቋማቱ ሰራተኞች ያለስጋት አገልግሎት እንዲሰጡ የክልሉን ሰላም በማረጋገጥ የፌዴራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት የማይተካ ሚና መጫወታቸውን ነው የገለጹት፡፡

የመንግስትን ጥሪ በመቀበል ስራውን የጀመረው ጽህፈት ቤቱም ባሉት ውስን ሠራተኞች ፋይሎችን በማደራጀትና የተሰባበሩትን በመጠገን ወደ ስራ በመግባት ለመቐለ ከተማ ህብረተሰብ አገልግሎት እየሰጠ እንዳለ አቶ ከበደ አሰፋ ገልፀዋል፡፡

የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ ብርድና ፀሀይ ሳይበግራቸው አገልግሎት ሰጭ ተቋማትን በመጠበቅ የህዝቡን የፀጥታ ሥጋቶች ከማስወገድ በዘለለ ቁጥጥርና ክትትል የሚያስፈልገውን የትራንስፖርት አገልግሎት በአራቱም አቅጣጫ ኬላዎች ህጋዊ እንቅስቃሴ እንዲፈጠርና ከታሪፍ ውጭ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎችን በማስተማር ፌዴራል ፖሊስ እየሰራ ስለመሆኑም ጠቁመዋል፡፡

ኃላፊው አክለውም የፌዴራል ፖሊስ የስራ ጫናን ለመቀነስ የክልሉ መንገድና ትራንስፖርት ቢሮ የክልሉን ትራፊክ ፖሊስና የመንገድ ትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ሰራተኞችን ወደ ስራ በማሰማራት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ስለመሆኑም የመቐለ ከተማ መንገድና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ከበደ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

ሰላም ወዳዱ የትግራይ ህዝብ ቀድሞ ወደ ነበረበት እንዲመለስ፣የታመሙ ህክምና እንዲያገኙ፣ልጆች እንዲማሩ የሁሉም ሰው ኃላፊነት መሆኑን በመገንዘብ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመቆም አስተማማኝ ሰላሙን ማረጋገጥ አለበት ሲሉ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ከፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.