ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከተመድ የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር ፊሊፖ ግራንዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ከፍተኛ ኮሚሽነሩ በትግራይ ክልል ያለውን የፀጥታና የመልሶ መቋቋም ሁኔታ የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸዉ ብዙ የሚያበረታቱ እንቅስቃሴዎችን ለማየት እንደቻሉ ገልጸዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በመሆን ከትግራይ ክልል ለተፈናቀሉና ለተሰደዱ ዜጎች ዘርፈ ብዙ እርዳታን ለመስጠት ዝግጅት ላይ መሆናቸውን መግለፃቸውን ከፕሬዚዳንት ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን