Fana: At a Speed of Life!

ዛሬ በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ ከሸፈ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 24 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ዛሬም በሁለት ተጨማሪ አካባቢዎች እሳት ለማስነሳት የተደረገው ሙከራ መክሸፉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡
በከተማው ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች እየታዩ ያሉ የእሳት ቃጠሎዎች በከተማው ህዝብና አመራሮች፣ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ሰራተኞች፣ የፀጥታ አካላትና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የጋራ ርብርብ የከፋ ጉዳት ሳያደርሱ መቆጣጠር ተችሏል ብሏል አስተዳደሩ።
የጥፋት አላማቸው ያልተሳካላቸው አካላት ሆን ብለው ህብረተሰቡን ለማሸበር እያደረጉት ያለው ተግባር እንደማይሳካም ገልጿል፡፡
ህብረተሰቡ ሳይደናገጥ ተገቢውን ጥንቃቄ እያደረገ፣ ሳይዘናጋ ነቅቶ አካባቢውን በመከታተል እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መረጃ በመለዋወጥ ያለምንም ስጋት መደበኛ እንቅስቃሴውን ማስቀጠል ይኖርበታልም ብሏል አስተዳደሩ ።
ከተማ አስተዳደሩ የጥፋት ተግባራትን በማክሸፍና ህብረተሰቡን ከአደጋ በመታደግ ላይ ላሉ ባለድርሻ አካላትና ነዋሪዎች ምስጋና አቅርቧል፡፡
እንዲሁም ከተማ አስተዳደሩ ለነዋሪው ችግር ቀድሞ የመድረስ ግዴታውን በአግባቡ እየተወጣ በመሆኑ እርስ በእርስ የመተጋገዝ አስቸጋሪ ወቅቶችን በጋራ የማለፍ ጉዞአችን በአብሮነት የሚቀጥል ይሆናል ብሏል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.