Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ ለአፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ገለፃ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ጥር 26፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለአፍሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በትግራይ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 
ሚኒስትሩ የአፍሪካ ህብረት በበይነ መረብ ባዘጋጀው 38ኛው የዋና ስራ አስፈፃሚ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ተሳትፈዋል።
 
ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ መንግስት በትግራይ ክልል የነበረውን ህግን የማስከበር እርምጃ ካጠናቀቀ በኋላ በክልሉ እየተከናወኑ ስለሚገኙ ስራዎች ነው ማብራሪያ የሰጡት።
 
ዜጎችን መልሶ ለማቋቋም እና ጉዳት የደረሰባቸውን መሰረተ ልማቶች መልሶ ለመገንባት እየተከናወኑ ስለሚገኙ ስራዎች ገለፃ አድርገዋል።
 
እንዲሁም ውጤታማ የሰብዓዊ ድጋፍ በትግራይ ክልል በማቅረብ የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር አቅም ለማሻሻል የተከናወኑ ስራዎችን አስመልክቶም ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
 
በዚህ የበይነ መረብ ስብሰባ ላይ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋቂ መሀመትን ጨምሮ የኮሚሽኑ የስራ ሃላፊዎች እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቹ ተሳትፈዋል።
 

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.