ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ በ34ኛው መደበኛ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እየተሳተፉ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 29፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ልዑካን ቡድናቸው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ እየተሳተፉ ነው፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአሁኑ ሰዓት በኢንተርኔት በመታገዝ በሚከናወነው 34ኛ መደበኛ የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች እና የርዕሳነ ብሔራት ስብሰባ ነው እየተሳተፉ የሚገኙት፡፡
የዘንድሮው ጉባኤ “ኪነ ጥበብ፣ ባህል እና ቅርስ የምንፈልጋትን አፍሪካ ለመገንባት” በሚል መሪ ቃል ይካሄዳል።
የህብረቱ መሪዎች ጉባኤ በተለያዩ አህጉራዊና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት ያደርጉበታል ተብሎ ይጠበቃል።
አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ ባመጣው የማህበረ ምጣኔ ሀብት ጫናን እንዴት ማገገም እንዳለባትም ሀሳብ ቀርቦ ሊወያዩበት እንደሚችሉ እየተጠበቀ ነው።
ዘንድሮ በይፋ ወደ ተግባር የገባው አህጉራዊው ነፃ የንግድ ቀጣና ወቅታዊ አፈጻፀም ላይም ውይይት እንደሚደረግ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!