Fana: At a Speed of Life!

የበረዶ ግግር መደርመስ ባስከተለው ከፍተኛ ጎርፍ ቢያንስ 14 ሰዎች ህይወታቸው አለፈ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በህንድ የሂማሊያ ተራራ የበረዶ ግግር ተደርምሶ ባስከተለው ከፍተኛ ጎርፍ በጥቂቱ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
በጎርፉ ሳቢያ ህይወታቸው ካለፈው በተጨማሪ 150 ሰዎች የገቡበት አልታወቀም ነው የተባለው፡፡
ከጠፉት መካከል አብዛኞቹ በአካባቢው በሚገኙት የውሃ ሀይል ማመንጫ የሚሰሩ ሰራተኞች እንደሆኑም ነው የተነገረው፡፡
ወታደሮችና ወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ለነፍስ አድን ስራ ወደ ስፍራው ተልከዋል ነው የተባለው ፡፡
የአካባቢው ባለሥልጣናት እስካሁን ከአደጋው 25 ሰዎች መትረፋቸውን ተናግረዋል፡፡
የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ በትዊተር ገፃቸው ያለውን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ምንጭ፡-ቢቢሲ
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.