ሰሜን ኮሪያ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ ዓመት የኒውክሌር መርሃ ግብሯን እንደቀጠለች ተመድ አስታወቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2013 (ኤፍቢሲ) ሰሜን ኮሪያ በተጠናቀቀው የፈረንጆቹ 2020 የኒውክሌር እና የባለስቲክ ሚሳዔል ፕሮግራሟን አጠናክራ መቀጠሏን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡
የኒውክሌር መርሃግብሯን ያጠናከረችው የተጣለባትን ዓለም አቀፍ ማዕቀብ ችላ በማለት ነው ተብሏል፡፡
ለመርሃግብሯ ይረዳት ዘንድም በበይነ መረብ ምንተፋ 300 ሚሊየን ዶላር ማግኘቷን ሪፖርቱ አስረድቷል፡፡
አዲሱ የአሜሪካ አስተዳደር ቃልአቀባይ በሰሜን ኮሪያ ጉዳይ አዲስ አቀራረብ እንደሚከተሉ አስታውቀዋል፡፡
በ2018 እና 2019 የአሜሪካ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጁንግ ኡን ሦስት ጊዜ ተገናኝተው መወያየታቸው የሚታወስ ነው፡፡
ስኬታማ ባልነበረው በዚህ ውይይት አሜሪካ ሀገሪቷ የኒውክሌር መርሃ ግብሯን እንድታቆም ስትጠይቅ ሰሜን ኮሪያ በበኩሏ ማዕቀቡ እንዲነሳላት ፍላጎት አሳይታለች፡፡
ሰሜን ኮሪያ አሁን ያሻሻለችው የረጅም እና የአጭር ባለስቲክ ሚሳኤል የኒውክሌር ተሸካሚ ሊሆን ይችላል የሚል ስጋትም ፈጥሯል፡፡
ምንጭ፡-አልጀዚራ
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!