አዲስ አበባ ከተሽከርካሪ ነጻ ቀን መርሃግብርን በመተግበር እና በሌሎች የመንገድ ማሻሻያዎች ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆነች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2013 (ኤፍቢሲ) አዲስ አበባ ከተማ ከተሽከርካሪ ነጻ ቀን መርሃግብርን በወር አንድ ቀን በመተግበር እና በሌሎችም የመንገድ ማሻሻየዎች የ2021 ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ሆነች፡፡
ሽልማቱ የዓለም አቀፍ ራዕይ ለዜሮ የመኪና አደጋ ተጋላጭነት ሽልማት ሲሆን፥ ከተሞች የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ በሚያደርጉት ጥረት የሚያገኙት ሽልማት ነው ተብሏል፡፡
አዲስ አበባም አደጋን ለመቀነስ የምታደርጋውን ጥረት ተከትሎ የ2021 የዓለም አቀፍ ራዕይ ለዜሮ የመኪና አደጋ ተጋላጭነት ለወጣቶች አመራር ሽልማትን ልትወስድ ችላለች፡፡
ምርጫው በአሜሪካው ብሄራዊ ማዕከል ለምቹ መንገድ ከዓለም አቀፉ የሞተር ስፖርት አካል ጋር በመሆን የተካሄደ መሆኑን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬታሪ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ከተማዋ ለወጣቶች እና ተማሪዎች የእግረኛ መንገድ አጠቃቀም ፖሊሲ በማውጣት እና በመተግበር ላሳየችው ተምሳሌታዊ ስራ፣ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ፍጥነትን ቀንሶ በማሽከርከር እና የትራፊክ አደጋ መቀነሻ ዘላቂ መንገዶችን በመተግበር ላስመዘገበችው ለውጥ እና ከተሽከርካሪ ነጻ ፕሮግራሞችን ይፋ በማድግ ያገኘችው ሽልማት ነው ተብሏል፡፡
በተጨማሪም በትምህርት ቤቶች አካባቢ የእግረኛ መጠቀሚያ መሰረተ ልማቶችን በማስፋፋት እና ከተሽከርካሪ ነጻ መርሐግብርን በወር አንድ ቀን በመተግበር የሰዎችን አስተሳሰብ በመቀየር የመኪና መንገዶች ለወጣቶች የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሆኑ በማድረግ ከተማዋ ለሰራቸው ስራ ይህን ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸናፊ ለመሆን መብቃቷ ነው የተገለጸው፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!