Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች በምርጫ ሥራዎች አፈጻፀምና የድህረ ምርጫ ሥራዎች ውጤታማነትን ከከተማዋ አመራሮች ጋር ገመገሙ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በምርጫ ሥራዎች አፈጻፀምና ድህረ ምርጫ ሥራዎች ውጤታማነትን የከተማዋ አመራሮች ጋር ገመግመዋል።

ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው÷ ዛሬ በምርጫ ሥራዎቻችን አፈጻፀምና የድህረ ምርጫ ሥራዎቻችን በውጤታማነት በመከወን የያዝናቸውን ግቦች በተሟላ መልኩ ከማሳካት አንፃር የተገኙ ውጤቶችን ከመላው የከተማችን አመራሮች ጋር ገምግመናል ብለዋል።

7ኛውን ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዳይጠናቀቅ ለማደናቀፍ በውጭም በውስጥም በጋራ በማበር በሚደያ ዘመቻዎች እና በተለያዩ ቅስቀሳዎች ሰላም የማደፍረስ ዝግጅቶችና ትንኮሳዎች ተደርገው ሳይሳካላቸው በኢትዮጵያ ታሪክ ትልቅ እድገት የታየበት ዴሞክራስያዊ፣ ሰላማዊና ተዓማኒ ምርጫ በማካሄድ ኢትዮጵያዊያን በፅናት አዲስ ታሪክ ፅፈው ኢትዮጵያ መርጣለች፥ ኢትዮጵያ አሸንፋለች ነው ያሉት።

እንደሀገር ያሳካነው እጅግ ውጤታማ እና ታሪካዊ ምርጫ የህዝባችን፣ የአመራራችን፣ የአባሎቻችን፣ የደጋፊዎቻችን፣ የሲቭክ ማህበራት፣ የሚዲያዎቻችን፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣

እንዲሁም በገለልተኝነትና በከፍተኛ ዲሲፕሊን ትልቅ ሀገራዊ ኃላፊነታቸውን የተወጡት የፀጥታ አካላትና የምርጫ ቦርድ በጥቅሉ ሁሉም ባለድርሻ አካል እንደ ሀገር ለዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ያለንን ቁርጠኝነትና በጋራ ያሳካነው ግብ መሆኑን ተግባብተናል ብለዋል።

ለዚህም ሁሉንም ባለድርሻ አካላት እናመሰግናለን ነው ያሉት ከንቲባዋ በመልዕክታቸው።

የድህረ ምርጫ ስራዎቻችን በውጤታማነት በመፈፀም ይህንን ፅኑ ህዝብ ለመካስ ያስቀመጥናቸውን ግቦች በተሟላ መልኩ ለማሳካት ከመላው አመራራችን ጋር ተግባብተናል ሲሉም ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.