Fana: At a Speed of Life!

የሀዌላ ቱላ-ወተራሬሳ-የዩ-ወራንቻ  መንገድ ግንባታ  ስራ በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሲዳማ ክልልን ከአጎራባች  የኦሮሚያ ክልል  ጋር በማገናኘት ከማዕከላዊ የደቡብ ኢትዮጵያ ጋር የሚያስተሳስረው  የሀዌላ ቱላ-ወተራሬሳ -የዩ-ወራንቻ  84 ነጥብ 7 ኪ.ሜ የአስፋልት መንገድ ግንባታ ስራ  በይፋ ተጀምሯል፡፡

ግንባታው በሶስት ዓመት ከስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሏል፡፡

በግንባታ ማስጀመሪያ ስነ ስርአቱ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ፣  የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ፣ የትራንስፖርት ሚንስትር ዴኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ ፣  የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ሀብታሙ ተገኘ ጨምሮ የፌደራልና የክልል የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ለመንገዱ ግንባታ 1 ቢሊየን 879 ሚሊየን 883 ሺህ 516 ብር ሲሆን የግንባታ ወጪው በኢትዮጵያ መንግስት ይሸፈናል፡፡

ጨረታ በማሸነፍ የግንባታ ስራውን የሚያካሂደው  የሥራ ተቋራጭ አገር በቀሉ ዮቴክ ኮንስትራክሽን  ድርጅት መሆኑ በስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡

የመንገድ ፕሮጀክቱን ጥራት ኢሲኢ ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ እና ዩኒኮን ኮንሰልቲንግ ኢንጂነርስ በጋራ በመቆጣጠር እና  በማማከር ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

በስላባት ማናዬ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.